Sunday, 3 November 2013

 ምንፍቅና ይቅርታ ይመልሰው ይሆን?......ሰሞንኛ 
“የበደልናትን ቤ/ክርስቲያን እንክሳለን፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤ/ክር ይቅርታ ታድርግልን፡፡ ”ተሀድሶያውያን፡፡……ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ በመታየት ላይ የሚገኘው የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመን ጉዳይ በእርቅ መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኘው ዘማሪት ፋንቱ ወልደ መሆኗ ታውቋል፡፡በጋሻውና ያሬድ አደመ ከላይ የተገለፀውን የተናገሩት ዘማሪት ፋንቱ ሁለቱንም ወደ “ብፅዕ አቡነ ገብርኤል” የሲዳማ፤ጌዲዮ፤አማሮ፤ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ እንደወሰደቻቸው ሲሆን እነበጋሻውም የአባታችን እግር ላይ በመውድቅ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ብፅዕነታቸውም “እኔን የሰደባችሁኝን በግሌ ይቅርታ ብያችኃለው የቤ/ክርስቲያንን ግን ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶሱ እየታየ ስለሆነ ውሳኔውን ከውደ በላይ ጠብቁ” በማለት መልስ ሰተዋል፡፡ዘማሪት ፋንቱ ማስታረቋን በመቀጠል እነበጋሻውን ወደ “ብፅዕ አቡነ ሉቃስ” የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ያቀረበች ሲሆን ብፅዕ አባታችንም “ሰው ይቅርታ ሲጠይቅ እንቢ አይባልም ይቅርታን መግፋት ተገቢ አይደለም ሆኖም ጉዳያችሁ አስቀድሞ በሲኖዶሱ የተያዘ በመሆኑ ትክክለኛውን ምላሽ ከዚያ ታገኛላችሁ” ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እነ በጋሻው ከሚቃረኗቸው ሰባኪያንና ዘማሪያን ጋር ቀርበው ለመነጋገርም ተስማምተዋል ህዝቡንም ቤ/ክርም ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡ይሁን እንጂ እንደ እኔ ከሆነ ቤ/ክርስቲያን ልትጠነቀቅባቸው የሚገቡ ጉዳዮችም አሉ ከይቅርታው ጋር ተያይዞ፡፡ ይህ ጉዳይ የመታረቅ እና ያለመታረቅ ጉዳይ አይደለም፡፡እነዚህ ሰዎች ከማንም በላይ ቤ/ክርንን አዋርደዋል፡፡ትምህርቷን በማጣመም በመበረዝ በክህደት ጎዳና ባለማወቅም ሆነ በማወቅ የነጎዱ ነበሩ፡፡ ብለው ብለው የጀመሩት ጎዳና የት እንደሚያደርሳቸው ሲያውቁ በይቅርታ ካባ መምጣታቸው ተገቢ አይደለም፡፡ ከልብ ተፀፅተው ከሆነም በቪሲዲያቸው፤በመፅሐፍቶቻቸውና በብሎጎቻቸው በመዝሙሮቻቸው ያስተላለፏቸው ኑፋኬዎች በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ፤ስራቸው ተመዝኖ ቅዱስ ሲኖዶስ መክሮበት ከሚሰጠው ውሳኔ በኃላ ይቅርታው መሆን አለበት፡፡ሌላው ይቅርና ግራና ቀኛቸውን ያልተመለከቱ ምዕመናንን በመያዝ ድንግል ማርያምን እና ቅዱሳንን ሲሰድቡ ለነበሩበት ሁኔታ እንኳን መልስ
የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም ገዳም ጎንደር የደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም የምትገኘው በጎንደር ከተማ በስተ ምዕራብ ከጎንደር ዪኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ተራራው አናት ላይ ትገኛለች:: የዚች ቤተ ክርስቲያንና ቤተ መንግሥት ጥንታዊ ስልጣኔ አሻራ የተጣለው በ 1730 ዎቹ በአፄ በካፋ ባለቤት በእቴጌ ምንትዋብ አማካይነት የተሠራ ሲሆን በግቢው ቤተ መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን ይገኝበታል፡፡ አመሠራረቱም ዐፄ በካፋ ከሞቱ በኋላ እቴጌ ምንትዋብ ልጃቸውን ኢያሱን አንግሠው ከዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ግቢ 2.5 ኪ.ሜ ራቅ ብለው የአራሳቸወን ቤተ መንግሥትና መኖሪያ አሰርተው ኑረውበታል:: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት በግብፅ በደብረ ቁስቋም ተራራ ላይ እንደተገኘች ሁሉ እቴጌ ምንትዋብም በቤተ መንግስታቸው ውስጥ ያሰሯትን ቤተ ክርስቲያን ቁስቋም ማርያም ብለው ሰይመዋታል ቤተ ክርስቲያኑንና ቤተ መንግሥቱን ለማሠራት አንድ ሺሕ ሁለት መቶ የሚደርሱ ግንበኞችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ባለሙያዎችን ለሁለት በመክፈል በሺፍት እንዳሰሯቸው ይነገራል:: በጊዜው ቤተ ክርስቲያኗ 200 በላይ ቀሳውስትና ካህናት አገልጋዮች ነበሯት፡፡ በ1881ዓ.ም. ደርቡሽ ጎንደርን ሲወር ጎንደር የሚገኙትን ብዙዎቹን ቤተ ክርስቲያናት ሲያቀጥልና ሲያወድም ካህናቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታቦት ከከተማ አርቀው ወደ በለሳ በማሸሽ አስቀመጡት፡፡ ደብረ ቁስቋም ቤተ ክርስቲያንም ሙሉ ለሙሉ ወደመች፡፡ ቤተ መንግሥቱንም ደርቡሽ አፈራረሰው፡፡ አብዛኞቹ ቅርሶችም ተዘረፎ ተቃጠሉ፡፡ ካህናቱም ወደተለያዩ ቦታዎች ተበታተኑ፡፡ ከጦርነቱ በኋላ ታቦቱን ወደነበረበት በመመለስ በጥቂት ካህናት ብቻ ለሰማኒያ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ከቆየ በኋላ በ1960ዎቹ ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሁን ያለውን ቤተ ክርስቲያን ታደሶ ተሰራ፡፡ ጥንታዊ ንዋየ ቅድሳን እና ቅርሶች፡- የእቴጌ ምንትዋብና የልጃቸው ኢያሱ፤ እንደሁም የኢያሱ ልጅ ኢዮአስን ዓፅሞች በአንድ ላይ በመሰብሰብ በሳጥን ውስጥ ተቀምጦ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም በሙዝየሙ ውስጥ ከሚጎበኙ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በሙዝየሙ ውስጥ የእቴጌ ምንትዋብና የልጆቻቸው በእንጨትና በቆዳ የተሠራ አልጋ፤ በቀርከሃና በቆዳ የተሠሩ የከበሩ ዕቃዎች ማስቀመጫ ቦርሳወች፤ ሚዛን፤ የደርቡሽ ጦር ካወደማቸው ሃይማኖታዊ የብራና መጻሕፍት የተረፉት ወንጌል ቅዱስ፤ ተአምረ ኢየሱስ፤ ግንዘት፤ ስንክሳር፤ ነገረ ማርያም፤ ሃማኖተ አበው፤ አሥራ አራቱ ቅዳሴያት፤ ግብረ ሕማማት፤ ገድለ ሠማዕታት ከበሮ፤ የተለያዩ መጠን ያላቸው መስቀሎች፤ ነጋሪት፤ እንዲሁም ከሙዝየሙ ውጪ በሩ አጠገብ የእቴጌ ምንትዋብ የድንጋይ ወፍጮ፤ እነዚህ ሁሉ ከደርቡሽ የተረፉ በሁኑ ወቅት ለጎብኚወች ክፍት የሆኑ ቅርሶች ናቸው፡፡ የቤተ መንግሥቱ ይዘት፡- ቤተ መንግሥቱ ሰባት በሮች ያሉት ሲሆን፡፡ የእቴጌ ምንትዋብ መኝታ ቤት፤ የገላ መታጠቢያ ቤት፤ ሣሎን፤ በዘመኑ የነበረው እንግሊዛዊው ታሪክ ጸሐፊው ጀምስ ፕሩስ /Jams prus/ መፀሀፍት ቤት እና ይኖርበት የነበረው ክፍል፤ ካህናቱና ቀሳውስቱ የሚመገቡበት የግብር ቤት፤ ቤተ ክርስቲያኑንና ቤተ ክርስቲያኑን ያነጹት ባለሙያዎች ማረፊያ ክፍሎችና ዕቃ ማስቀመጫ ክፍሎች፤እዲሁም የእቴጌ ምንትዋብ የካባቢውን ሴቶች ባልትና ያስተምሩበት ክፍል ጣራወቹ ወድመው ፈራርሰው ይታያሉ፡፡ የእቴጌ ምንትዋብ ቤተ መንግሥቱ ያሰሩባቸው ቁሳቁሶች መካከል ኖራ፣ ወይራ፣ ዝግባ፣ ግማርዳ ..... እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ተጠቅመዋል:: በአንድ ወቅት እቴጌ ምንትዋብ በግብር ቤታችው ካህናቱና ቀሳውስቱ ግብዣ ጠርተው ያስቀረቡት ምግብና መጠጥ ቀሳውስቱ እንደ ጠበቁት ባለመሆኑ እቴጌን በቅኔ ሊነግሯቸው ፈለጉና ግብር ቤቱ ክተሰራበት እንጨት አንዱን መረጡና ንግስት ይሂ እንጨት ምን ይባላል ይሏቸዋል እቴጌም ይህማ ግማርዳ ይባላል ይሉና ይመልሳሉ:: ነገሩ ቆይቶ የገባቸው እቴጌ በሌላቀን የሞቀ ድግስ ይደግሱና ካህናቱና ቀሳውስቱ ግብዣ ጠርተው በልቶ ጠጥቶ ወጦ መመለስ ክልክል ነው ብለው በጠጅ እና በጮማ ያጠግቧቸዋል:: ከጠጁ ብዙ ለመጠጣት ለሺንት መውጣት ባለመቻላቸው ከቀሳውስቱ መካከል አንዱ በመነሳት እቴጌን በቅኔ አምስት መቶ እና አምስት መቶ ስንት ነው ይሏቸውና እቴጌም መልሱ የቀለላቸው መስሏቸው ‘’አምስት መቶ እና አምስት መቶማ ሺ ነዋ’’ በለው ይመልሉ:: ይሂን መልስ የፈለጉት ተጋባዢ ‘’እረ ንግስት ሺናው’’ ብለዋል ብለው እቴጌን እዳሸነፏቸው ይነገራል። አሁንም ይህ የግብር አዳርሽ ሺናው አዳርሽ እየተባለ ይመራል:: የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የማይነጥፍ ታሪክ ባለቤት ነች:: የጎንደር ደብረ ፀሐይ ቁስቋም ማርያም ለማሰተዋወቅ ያህል ባችጭሩ ይሂን ይመሰላል:: ይቆየን አቱ ሶል
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ኅዳር 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ሊቀ ልሣናት ቀሲስ ከፍያለው ጥላሁን ሥነ ምግባር፡- ማለት ደግነት፣ በጎነት፣ መልካም ጠባይ ማለት ሲሆን ክርስቲያን የሚለው ቃል ሲጨመርበት ደግሞ የተሟላና የተለየ ያደርገዋል፡፡ መልካም ጠባይ ማንም ሰው ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የተሟላ ዘላቂና የሁል ጊዜ ሆኖም ለሰማያዊ መንግሥት የሚያበቃው በክርስትና እምነት ሲኖሩ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፡- በምድር እያለን ሰማያዊ ኑሮ ኖረን ለሰማያዊ መንግሥት የምንበቃበት ሕይወት ነው፡፡ ሰውን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማስደሰት ነውና፡፡ በመሆኑም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በሚከተሉት ሕግጋት ሊለካ ይችላል፡፡ 1. ሕገ እግዚአብሔር መጀመሪያውና ዋነኛው የክርስቲያን ሥነ ምግባር መለኪያው ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ አንድ ሰው ምናልባትም ሕይወቱ በሰው ፊት ሲታይ የማያስደስት በአፍአ ያለው ጠባዩ እንከን የማይወጣለት ሊሆን ይችላል፡፡ በሕገ እግዚአብሔር ተመዝኖ ካላለፈ ዋጋ የለውም በሰው ፊት መልካም ሆኖ የሚታይ ምግባር እግዚአብሔርን ሊያስደስት ያስፈልጋል፡፡ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፡፡” ፌፌ.6፥6 ፈሪሳውያን ከእነርሱ ውጪ የሆነውን ሁሉ የናቁ ያለእኛ ሕገ እግዚአብሔርን አክባሪ ከእኛም በላይ ጻድቅ የለም ባዮች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግብዞችና ሥራቸው ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ነገራቸው፡፡ እንዲያውም “ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም” ማቴ.5፥20 በማለት ደቀ መዛሙርቱን አስጠነቀቀ፡፡ እንዲያውም ከእነርሱ እርሾ /ትምህርት/ እንዲጠበቁ አስጠነቀቃቸው፡፡ “ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ” ማቴ.16፥6 አለ፡፡ ከዚህም ሌላ ብዙ ሠርተናል ሥነ ምግባራችን አስደሳች ነው እያሉ ለመወደስ በኩራት ይቀርቡ የነበሩትን ሁሉ አፍረው እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ ማቴ.19፣16-22 የንጉሥ ሳዖል ሥራ በራሱ በንጉሡ አሳብ ሲመዘን ምክንያታዊና ትክክልም ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን ሊያስደስት አልቻለም፡፡ ቃሉን ስላላከበረ ለእርሱም ስላልታዘዘ ንቀኸኛልና ንቄሃለሁ ተባለ፡፡ ከንግሥናውም ወረደ፡፡ 1ሳሙ.15፥10-22 “ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡” ዕብ.11፥6 ክርስቲያን በጉዞው ሁሉ በጭፍን በራሱ እውቀት ብቻ አይመራም፡፡ በቃለ እግዚአብሔር ሕይወቱን እየመዘነ ሊራመድ ያስፈልጋል፡፡ “በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ ራሳችሁን ፈትኑ፡፡” 2ቆሮ.13፥5 የክርስትና እምነት እያጸኑና እየጠነከሩ እየበሰሉ የሚጓዙበት ሕይወት ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ክርስቲያን ከትላንት ዛሬ ከአምና ዘንድሮ አድጐ ጠንክሮ መገኘት አለበት፡፡ “ንቁ በሃይማኖት ቁሙ ጐልምሱ ጠንክሩ” 1ቆሮ.16 በሃይማኖት መጠንከር ሲባል በጊዜውም /በተመቸ ጊዜ/ አለ ጊዜውም /ባልተመቸ ጊዜ/ መጠንከር ይገባል፡፡ “በጊዜውም አለ ጊዜውም ጽና፡፡” 2ጢሞ.4፥2 እንዲል፡፡ ከሰው ሕግ ይልቅ የእግዚአብሔር ሕግ ቅርብ ነው፡፡ ከሰው ሕግ መደበቅ መሸሽ ይቻላል፡፡ ከእግዚአብሔር ግን ማምለጥ አይችልም፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ሥራ በእርሱ ዘንድ የተገለጠች ናት፡፡ የጲጥፋራ ሚስት ዮሴፍን ማንም አያየኝም ኀጢአት እንሥራ ብላ ለሁለት ዓመታት ባባበለችው ጊዜ ኩፋ.27፥25 እግዚአብሔር ከእርሱ እንደማይለይ እያንዳንዱም ሥራው በፊቱ የተገለጠ እንደሆነ ያመነው ኀጢአትን እንዴት እሠራለሁ በማለት መለሰለት፡፡ ዘፍ.39፥9፣ መዝ.138፥2-12 ስለዚህ ክርስቲያናዊ አኗኗራችን መልካም ምግባራችን ትክክለኛ የሚሆነው በእግዚአብሔር ሲመዘን ብቻ ነው፡፡ ብልጣሶርን “በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ” ዳን.5፥27 የተባለው ለዚህ ነው፡፡ የሰው ልጁ ሕግ ተለዋዋጭና ጊዜያዊ ነው፡፡ ሕገ እግዚአብሔር ግን በዘመናት ብዛት የማይሻርና ቋሚ በመሆኑ ምግባራችን ከዚህ አንጻር ሊለካ ያስፈልጋል፡፡ “እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ፡፡ ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሠላም ነው፡፡” ሮሜ.8፥5‐6 2. ሕገ ልቡና እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው ከሌሎች ፍጥረታት በተለየ ሁኔታ የሚመራመር ክፉና በጎውን ለይቶ የሚያውቅ አእምሮ ሰጥቶታል፡፡ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፡፡” መዝ.139፥10 እንዲል፡፡ በተጨማሪም “ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው፡፡”መዝ.118፥105 ብሏል፡፡ ሕግ ለሙሴ ከመስጠቱ በፊት ደጋግ አባቶች በዚህ ሕግ እየተመሩ እንደሚገባ ኖረዋል፡፡ የሰው ልጅ ማንም ባያስተምረውና ባይነግረው የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ያውቃል፡፡ “እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን እያንዳንዱም ወንድሙን እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና ይላል እግዚአብሔር፡፡” ኤር.31፥34 ምሳሌ አቤል “ከበጎቹ በኩራትና ከላቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ ወደ ቃየል እና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም፡፡” ዘፍ.4፥4-5 ሄኖክ “አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና፡፡” ዘፍ.5፥24 ኖኅ “ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘ በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡” ዘፍ.6፥9 እነዚህና ሌሎችም በሕገ ልቡና ተመርተው መልካም ተግባር የፈጸሙና እግዚአብሔርም ሥራቸውን የወደደላቸው ናቸው፡፡ ዕብ.11፥4-7 የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር በራቀ ቁጥር ግብሩ ወደ እንስሳነት ይለወጥና የሚወቅሰው ኅሊና እንኳን ያጣል፡፡ “የሰው ልጅ ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ፡፡” መዝ.48፥12 ናቡከደነፆር በበደል ላይ በደል በመጨመሩ ለእግዚአብሔር ሕግ አልገዛም በማለቱ ግብሩ ሁሉ የእንስሳ ሆነ፡፡ ዳን.4፥32 ስለዚህ ክርስቲያን በመጽሐፍ ከተዳፈነው የእግዚአብሔር ሕግ በተጨማሪ በልቡናው ለተቀረጸው ሕግ ይገዛል፡፡ ራሲንም እየመረመረ ይጓዛል አጥፍቶም እንደሆነ ማንም ሳይፈርድበት በራሱ ላይ ይፈርዳል፤ ንስሐ ይገባል የጠፋው ልጅና በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ ለዚህ ምስክር ይሆኑናል፡፡ ሉቃ.15፥11-19፣ ሉቃ.23፥41 3. የሰው ሕግ ይህን በሁለት ከፍሎ መመልከት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው የአንድ ሀገር መንግሥት ወይም የሚያስተዳድር አካል ሕዝቡን ለማስተዳደር የሚያወጣው ሕግ ከሆነ ሁለተኛው ደግሞ ኅብረተሰቡ በባሕሉ ትክክል ነው ብሎ የተቀበለውና በወረቀት ያልተጻፈው ሕግ ነው፡፡ “በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ” 2ተሰ.2፥15 እንዲል፡፡ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ሕግ እንደሚገዛ ሁሉ የሰውንም ሕግ ከእግዚአብሔር ጋር እስከ አላጣላው ድረስ ሊያከብር ይገባል፡፡ አንድ ሰው ምንም ብጾም ብጸልይ፣ ለእግዚአብሔር እገዛለሁ ቢል የሚያስተዳድረውን አካልና የኅብረተሰቡን መልካም ባሕል ካፈረሰ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባሩን ጎደሎ ያደርገዋል፡፡ በሥራ ቦታ የታዘዘውን ካልፈጸመ፣ የሥራ ሰዓት ካላከበረ፣ በቤተ ክርስቲያን ያለውን ምግባሩን በሌላ ሥፍራ ካልገለጸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ለእግዚአብሔር እንደሚገዛ ሁሉ በሰውም ፊት ያለነቀፋ ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ “በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ በእነርሱም መካከል የሕይወት ቃል እያቀረባችሁ በዓለም እንደ ብርሃን ትታያላችሁ” ፊል.2፥15 ሐዋርያው ከዚህም በተጨማሪ “ማንም እንዳይነቅፈን እንጠነቀቃለን በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን እናስባለን” ብሏል፡፡ 2ቆሮ.8፥20 ይህ ሲባል ኀጢአትም ሲሆን የሰው ሕግ ወይም ባሕል ነውና ሁሉን መፈጸም አለበት ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ በላይ ማግባት፣ ጫት መቃም፣ ዋርሳ መያዝ፣ ባሕል በሆነበት አካባቢ የሚኖር ክርስቲያን ከሰው ጋር ለመኖር በሚል ሰበብ ይህንና ይህን የመሰለ የአረማውያኑን ኑሮ ይኑር ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ክርስቲያን በእንዲህ ዓይነት ሰዎች መካከል ሲኖር የቅድስናን ሕይወት በተግባር በመኖር ማንነቱን ሊገልጥ ያስፈልጋል፡፡ “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡” ማቴ.5፥16 ከዚህ አንጻር ብዙ ወጣቶች ሕገ እግዚአብሔርን ከኑሮአቸው ጋር አጣጥመው መጓዝ ሲከብዳቸው ይታያሉ፡፡ በእምነት የጸኑትን ሠለስቱ ደቂቅን፣ ዮሴፍን ሶስናን አይመለከቱም፡፡ እንኳን ክርስቲያን የሚለውን ስም የተሸከሙ ሲጠራም የሰሙት የማይመስሉ አሉ፡፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በሰውና በእግዚአብሔር ፊት የምንኖረው ኑሮ እንደመሆኑ መጠን የግል መንፈሳዊ ሕይወትና ማኅበራዊ ኑሮ በማለት በሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን፡፡ ሀ. የግል መንፈሳዊ ሕይወት፡- የግል መንፈሳዊ ሕይወት ማለት እኛ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት የሚኖረን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖረን ግንኙነት ይመሠረታል፡፡ አንድ ሰው ፍቅሩ እግዚአብሔር ከሆነ ምግባሩ መንፈሳዊ ሕይወቱ ይህንኑ የሚገልጥ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረው ሕይወት የጠበቀ ለማድረግ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ ቃለ እግዚአብሔር፣ ንስሓ፣ ቅዱስ ቁርባን፣ ጸሎት ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡ ቃለ እግዚአብሔር ለአንድ ክርስቲያን የሕይወት መስመሩን የሚያቃናለት ነው፡፡ “ቃልህ ተገኝቷል እኔም በልቸዋለሁ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ በስምህ ተጠርቼአለሁና ቃልህ ሐሴትና የልብ ደስታ ሆነኝ፡፡” ኤር.15፥16 ንስሓ ማለት መጸጸት ማለት ነው፡፡ የክርስትና ሕይወት የንስሓ ሕይወት ነው፡፡ በንስሓ የበደለ ከበደሉ ይነዳል፡፡ ኀጢአተኛውም ጻድቅ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለግል መንፈሳዊ ሕይወት ሥራችሁን አቅኑ፡፡” ኤር.18፥11 ከንስሐ በኋላ ቅዱስ ቊርባን መቀበል ያስፈልጋል፡፡ “የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ ሕይወት የላችሁም፡፡” ዮሐ.6፥53 እንግዲህ ቃሉን ሰምተን ንስሓ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ስንቀበል የግል መንፈሳዊ ሕይወታችን የተስተካከለ ይሆናል፡፡ የግል መንፈሳዊ ሕይወት ጽናት ደግሞ ለማኅበራዊ ኑሮአችን ወሳኝ ነውና፡፡ “ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አሳብ ይህንም አዘውትር፡፡ ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፡፡ በእነዚህ ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ፡፡” 1ጢሞ.4፥15 ለ. ማኅበራዊ ኑሮአችን ክርስቲያን በማኅበራዊ ኑሮው ከሌሎች ጋር በሠላምና በፍቅር ሊኖር እንዲሁም አልጫውን ዓለም በምግባሩ ሊያጣፍጥ ይገባል፡፡ በመሆኑም ክርስቲያን በማኅበራዊ ኑሮ ተሳትፎ ውስጥ ሊይዝ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህም፡-
 ዓላማ፡- ክርስቲያን እንደ ውኃ ላይ ኩበት እየተንሳፈፈ ወንዙ ወደ ሚወርድበት አቅጣጫ አይጓዝም፡፡ እንደሚወዛወዝ ዛፍም ወደ ነፈሰበት አያጋድልም፡፡ የራሱ የሆነ ውሳጣዊ ዓላማና አቋም አለው፡፡ “በምትሄድበት ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፡፡” ኢያሱ.1፥7 ከዚህ የተነሣ የሚሠራውን በጽናትና በትጋት ይሠራል፡፡ የጀመረውን ከፍጻሜ ያደርሳል፡፡ በመከራ አይናወጥም፡፡ መስሎ ለማደር እንደ ጊዜው አይለወጥም፡፡ በዓላማ ስለሚጓዝ ዓላማውን ያሳካል፡፡ ክርስቲያን ምን ዓይነት ዓላማ ሊኖሩት ያስፈልጋል? መንግሥተ ሰማያትን መውረስ፡- አንድ ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣው ለጊዜያዊ ችግሩ ብቻ መፍትሔ ለማግኘት አስቦ ሳይሆን ሰማያዊ ክብርና ዋጋ ለማግኘት ነው፡፡ “ድንኳን የሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘለዓለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንፃ እንዳለን እናውቃለን፡፡ 2ቆሮ.5፥1 የሚታወቅና ግልጽ ዓላማ፡- ክርስቲያን ያለ ዓላማ በጭፍን አይጓዝም፡፡ ሳይታሰብ በድንገት በአጋጣሚ የሚል ነገር በርሱ ዘንድ እምብዛም ቦታ አይኖረውም፡፡ የሚታወቅ ግልጽ ዓላማ ኖሮት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሳካለት ይጸልያል፡፡ “ሳታቋርጡ ጸልዩ፡፡” 1ተሰ.5፥18 ከዚህ አንጻር አንዱን ዓላማው አድርጎ ይጓዛል ጋብቻ ወይም ምንኩስና መካከል ሆኖ አያወላውልም፡፡ ራስን መግለጽ፡- ክርስቲያን በሄደበት ሁሉ ማንነቱን መግለጥ አለበት፡፡ በተራራ ላይ ያለች ከተማ መሰወር አትችልም፡፡ ይህም ሲባል እኔ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ እያለ በማወጅ ወይም በማስታወቂያ ሳይሆን አኗኗሩ ማንነቱን ይገልጠዋል፡፡ ይህም ኑሮው በቤተሰብ፣ በት/ቤት፣ በሥራ ቦታ፣ በአካባቢው ኅብረተሰብ ዘንድ ወዘተ…… መገለጥ አለበት፡፡ ታማኝነት፡- እውነተኛ ክርስቲያን ምሎ የማይከዳ፣ አደራ የማያጠፋ፣ የማያወላውል ለምስክርነት የሚበቃ ነው፡፡ ታማኝ ሰው መልካም የሚለውን ይናገራል፡፡ የሚናገረውን ይሠራል በሓላፊነት ቢቀመጥ ያለ አድልዎ ወገናዊነት ያስተዳድራል፡፡ “በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሀለሁ፡፡” ማቴ.25፥21 ይባልለታል፡፡ ታማኝነት ለራስ ታማኝ መሆን ለእግዚአብሔር ሰዎች በመታመን ይገለጣል፡፡ ይህም በትዳር፣ በሥራ፣ በተሰጠው ሓላፊነት መታመን አለበት፡፡ ምሳሌ ዮሴፍ ዘፍ.39፥9 ፍቅር፡- ክርስቲያናዊ ፍቅር የያዘ ሰው በሰውና በእግዚአብሔር ፍቅር ያለነቀፋ ይኖራል፡፡ ፍቅር የክርስቲያንነታችን መገለጫ ነው፡፡ አምላክን ከዙፋኑ ያወረደው ራሱንም እስከ ሞት አሳልፎ ለሰው ልጅ እንዲሰጥ ያደረገው ፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ አንደ ሰው ፍቅር ከሌለው ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የለውም ማለት ይቻላል፡፡ የምናፈቅረው ማንን ነው? እግዚአብሔርን፡- እግዚአብሔርን ማፍቀር ሲባል እግዚአብሔርንና የእርሱ የሆነውን ሁሉ ማፍቀር ማለት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ፍቅረ እግዚአብሔርን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ 1. ትእዛዙን ማክበር፡- እግዚአብሔርን መውደድ ትእዛዛቱን በመፈጸም ይገለጣል፡፡ “ትእዛዙ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው፡፡” ዮሐ.14፥21 2. የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ መውደድ ይህን በሦስት ከፍለን መመልከት እንችላለን 2.1. ቅዱሳንን መውደድና ማክበር፡- ቅዱሳን እግዚአብሔር የመረጣቸው ያከበራቸውና የወደዳቸው ናቸው፡፡ “የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና አስቀድሞ የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው የጠራቸው እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው ያጸደቃቸው እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፡፡” ሮሜ.8፥29 ፍቅረ እግዚአብሔር የእርሱ የሆኑ ቅዱሳንን በማክበር እንገልጻለን፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር የትሕትናና የኦርቶዶክሳዊነት ውጤት ነው፡፡ 2.2. ሀገርን መውደድ፡- ሀገር የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን እግዚአብሔር በሰጠው ሀገር ሆኖ እርሱን ሊያመሰግን ሀገሩን ሊወድ ግዴታ አለበት፡፡ ሀገር ከሌለ ሠላም ካልሆነ እግዚአብሔርን በደስታ ማመስገን አይቻልምና፡፡ “ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ ባላስብሽ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድ፡፡” መዝ.136፥5 2.3. ቤተሰብን መውደድ፡- ክርስቲያን እምነትን፣ ምግባርን፣ ሥርዓትን በመጀመሪያ የሚማረው ከቤተሰቡ ነው፡፡ ቤተሰብ የመጀመሪያዎቹ ትምህርት ቤቶች ናቸው፡፡ ነቢዩ ሙሴ የእግዚአብሔርን፣ የወገንን፣ የሀገርን ፍቅር የተማረው ከእናቱ ነውና፡፡ ወልደው፣ አሳድገው፣ አስተምረው ለትልቅ ደረጃ ያበቁትን ቤተሰቡን ክርስቲያን ሊወድ ይገባዋል፡፡ “ስለ ቤተሰቦቹ የማያስብ ማንም ቢኖር ሃይማኖትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡” 1ጢሞ.5፥8 3. የሰው ልጆችን ሁሉ ማፍቀር፡- /ፍቅረ ቢጽ/ የሰውን ልጅ ሁሉ ማፍቀሩ ፍቅረ ቢጽ ይባላል፡፡ ይህም በሥላሴ አርአያ የተፈጠረውን ሰው ሁሉ መውደድና ማፍቀር ነው፡፡ ይህም ኀጥእ ጻድቅ፣ አማኒ መናፍቅ፣ ዘመድ ባዕድ ሳይሉና ሳይለዩ  ሁሉን አስተካክሎ መውደድ ነው፡፡ ይህም ትእዛዝ ጠላትን እስከመውደድ በመድረስ ነው፡፡ “በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚጠሏችሁ መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ፡፡” ማቴ.5፥44 በአጠቃላይ ክርስቲያን ከአለባበሱ ጀምሮ ውጫዊ አቋሙም ሆነ አጠቃላይ ሕይወቱ በማናቸውም ጊዜና ቦታ ሁሉ ክርስቲያንነቱን ሊገልጡ ይገባቸዋል፡፡ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ኖረው ለሰውም ብርሃን ሆኖ እግዚአብሔርንና የእግዚአብሔር የሆኑትን አስደሰተ የሚባለው ያን ጊዜ ነው፡፡ እንግዲህ ክርስቲያን በምድር ሲኖር በግል ሕይወቱም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮው ምን መምሰል እንዳለበት ራሱን ከላይ በተገለጸው በሦስቱ ሕግጋት አንጻር እየመረመረ መጓዝ አለበት፡፡ በግል ሕይወቱ ዘወትር ንስሓ እየገባ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል እየጾመ፣ እየጸለየ፣ እየመጸወተ ሰማያዊ መንግሥትን ተስፋ በማድረግ ይጓዛል፡፡ በማኅበራዊ ኑሮውም ደግሞ ሰዎችን በሐዘናቸው ጊዜ ማጽናናት፣ በደስታቸው ተካፋይ መሆን፣ ከቸገራቸው ለችግራቸው ደራሽ በመሆን እውነተኛ ፍቅሩን ሊገልጽ ያስፈልጋል፡፡ “የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁል ጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን፡፡” 2ቆሮ.4፥10




















                                                                                እያወቁ አለቁ? 
ቀድሞ ከአስርና ከሃያ ዓመታት በፊት ቤተ ክርስቲያኒቱን በቅርቡ የማያውቋት ወገኖች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም ከወንጌል ያፈነገጠች ፤ ባህላዊ ነገር የሚበዛባት ፤ ከወንጌል ጋር ግንኙነት የሌላት አድርገው ይሰብኩ ነበር ፡፡ ይህ አካሄድ እንደማያዘልቃቸው የተረዱት ወገኖች ቀስ በቀስ በመንሸራተት ቤተክርስቲያን ያስቀመጠችውን ስርዓት በመውሰድ ሲጠቀሙ እየተስተዋሉ ይገኛሉ ፡፡ ማንም ባይጠይቃቸውም ከበሮውን ፤ ጽናጽሉን ፤ መቋሚያውን ፤ እና መሰል መገልገያዎችን ወደ አዳራሾቻቸው ካስኮበለሉ ቆይተዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአገልጋዮቿ የምትሰጠውን የማዕረግ ስም መጠቀም ከጀመሩም ሰንበትበት ብለዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድን ዜማ ቤተ ክርስቲያን ባስተማረቻቸው ሰዎች አማካኝነት አባሎቻቸውን በማስተማር ፍጹም አይን ያወጣ ዝርፊያ በማድረግ እንደ ተሐድሶያውያን መዝሙር መሳይ ዘፈኖቻቸውን መስራት ጀምረዋል ፤ ምንም የግጥምም ሆነ የዜማ ለውጥ ያልተደረገባቸው መዝሙሮቻችን የአዳራሾቻቸው ማሞቂያዎች ከሆኑ ቆይተዋል ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በበገና የታጀበ መዝሙር ለገበያ አቅርበዋል ፤ ስብከቶቻቸው ላይም ስለማያውቁት ቅዱስ ያሬድ በማንሳት ሰማያዊ ጸጋን ከአምላክ መቀበሉን እየሰበኩ ይገኛሉ ፤ .. ታዲያ እኝህ ሰዎች ምን ቀራቸው ? በነገራችን ላይ አሰላ የሚገኙ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በ40 እና በ80 ቀን በአዳራሾቻቸው ልጆቻቸውን ክርስትና ማስነሳት መጀመራቸውን ሰምተናል ፡፡ እኔን የገረመ የ40 እና የ80 ቀን በማለት ቤተክርስትያን ልጇቿ የሥላሴ ልጅነትን የምትሰጥበት ትርጉሙን አንብበውም ይሁን ከሰው ጠይቀው ሊያውቁት ይችላል ፡፡ ግን ልጆቹን ሲያጠምቁ ምን አይነት ጸሎት እንደሚያደርጉላቸው ማወቅ ነበር የሚያጓጓው ፤ ማን ያውቃል ያስኮበለሉት አገልጋይ ሊኖርም ይችላል ፡፡ ቄስ በሪሁን የዛሬ ዓመት ከነጋድረስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ራሱን ሲያስተዋውቅ “ቄስ በሪሁን እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት ወሎ ክፍለ ሀገር ነው፡፡ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርን በአዲስ አበባ እና ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ፡፡ እንደ ማንኛውም ወጣት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው ያደኩት፡፡ መካነ ኢየሱስ አጠገቤ ስለነበረች የወንጌል ሙቀትን ከሷ ነው ያገኝሁት” በማለት ነበር ራሱን ያስተዋወቀው፡፡ ይህው ሰው ከጌሤም መጽሔት ቅጽ 3 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም ዕትም ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር፡፡ ቃለ መጠይቁን እንዲህ ነበር ጌሤም፡- የአሁን ወደ አዲስ አበባ አመጣጥ ለእረፍት ነው ወይስ ለተለየ እቅድ አለህ? “እንግዲህ የአሁኑ ጉዞዬ ትንሽ ለየት ያለ ነው ፡፡ በኢቢኤስ ለስምንት ወር ያህል በተከታታይ ስናገርበት የነበረና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአብይ ጾም በአንድነት እንድንጾም በአብይ ጾሙ ዙሪያ ላይ የሚመለከታቸው ሰዎች ለማነጋር 2005ትን አብይ ጾም አብረን በመላው አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ስለሀገራችን ፤ ስለህዝባችን ፤ ስለወንዞቻችን ፤ ስለተራሮቻችን ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ ቃለ እግዚአብሔር በሚያዘው መሰረት ወደ እግዚአብሔርፊት በሥላሴ የምናምን በሙሉ እንድንቀርብ ለማስተባበር ነው የመጣሁት፡፡ ይህንን ጉዳይ ብዙ ሕዝብ ሰምቶት አስተያየታቸውንም በስልክ ፤ በኢሜል ለእኔም አሜሪካ ሀገር ባለኝ ኢሜልና አድራሻዬ ስልክ እንዲሁም ደግሞ አዲስ አበባ ባለው ቢሯችን በስልክ ምላሽ ሰጥቷል ፤ ጥያቄዎችንም አብራርቼአለሁ አሁንም ይቀጥላል፡፡ ……….የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነች ፡፡ ረዥም ዓመት በወንጌል አገልግሎት የቆየች ቤተክርስቲያን ነችና ባህላዊውንም ከወንጌላውያን የተሻለ ዓይነት ሁኔታ ታውቃለች፡፡ ታሪካዊ አመጣጧ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይህን ያህል ዘመን ጸንቶ ፆሙ የመቆየቱ ሁኔታ የጥንካሬው ምክንያት የቤተክርስቲያቱ ሊቃውንቶች ቢያብራሩት ይሻላል፡፡” በማለት መልሷል፡፡ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምን ቀራቸው?
እግዚአብሔር እንዲረዳን ሁሌ ስለቤተክርስቲያን እና ስለ ምዕመናን እንጸልይ:: ይህን የመነቃቃት እና የፍትህ ዘመን ስንናፍቀው ነበር ፤፤ ሁሉም ነገር በጊዜው ነውና እነሆ ዛሬ እውነተኛ አባቶች እንደገና በመፈጠራቸው በጣም ተደስተናል ፡፡ ቤተክርስቲያን የተዋረደችበትና በአደባባይ ስማ እየተነሳ መሳለቂያ የሆነችበት እንደዚህ ያለ ዘመን ከቶ የለም ፤ አላታየም ፡፡ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ ፤ የመሬት መነጠቅ፤ የካህናት መገደል(መታረድ) ፡ የምዕመናንን መገደል (መታረድ) ፤ የአምልኮ ቦታ መከልከል…………. ፤፤ ይሄ ሁሉ በደል እንዴት አንድ ህግ ባላት ሀገር ውስጥ ይፈጸማል // ይህም የሆነው ለቤተክርስቲያን እና ለምዕመናን የቆመ እና ሰማያው የሆነውን አባታዊ አደራውን የረሱ አባቶቸ ስለተበራከቱ ነው ፡፡ እናንተን እውነተኛ አባቶቸን ግን እግዚአብሄር ስለሰጠን ኮርተንባችሀል ፡፡በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ህልውናዋ እና መብታ እንዲረጋገጥ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያለ ቆራጥ መሪ እና ለእውነት የቆመ አባት ያስፈልገናል ፡፡አቡነ ጴጥሮስን ታሪክ የሚዘክራቸው አባት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውን ስለእውነት አሳልፈው ስለሰጡ ጭምር ነው ፡፡... እባካችሁ አባቶች ይህ በደል እና ግፍ ታስቦ እና ተቀነባብሮ ቤተክርስቲያን ለማዳከምና ህልውናዋን አደጋ ላይ ለመጣል ሆን ተብሎ በሁሉም ቦታ እየተሰራ ያለ ሴራ ስለሆነ እውነተኛ ፍትህ እስክታገኙ ድረስ ወደ ኀላ እንዳትመለሱ ፡፡ በመድረኩ ላይ ያልተነሱ ብዙ ከባድ እና አስከፊ በደሎችም ስላሉ ወደ ታች ወርዳችሁ ምዕመናንን ማማከር እንዳትዘነጉ ፡፡ ይህ ነገር የአንድ ሰሞን ግርግር ብቻ ሆኖ እንዳይቀር አደራ እላለው ፡፡ ምእመናንም ይህንን ግፍ በዝምታ እና በትዕግስት ማለፍ ይብቃን እላለው ፡፡ ህግ ባላት ታላቅ ሀገር ስላላን የህግ ያለህ እንበል /// ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡ በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም›) እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው››) አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡››)አለቻት አሉ፡፡