Sunday, 3 November 2013

                                                                                እያወቁ አለቁ? 
ቀድሞ ከአስርና ከሃያ ዓመታት በፊት ቤተ ክርስቲያኒቱን በቅርቡ የማያውቋት ወገኖች ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም ከወንጌል ያፈነገጠች ፤ ባህላዊ ነገር የሚበዛባት ፤ ከወንጌል ጋር ግንኙነት የሌላት አድርገው ይሰብኩ ነበር ፡፡ ይህ አካሄድ እንደማያዘልቃቸው የተረዱት ወገኖች ቀስ በቀስ በመንሸራተት ቤተክርስቲያን ያስቀመጠችውን ስርዓት በመውሰድ ሲጠቀሙ እየተስተዋሉ ይገኛሉ ፡፡ ማንም ባይጠይቃቸውም ከበሮውን ፤ ጽናጽሉን ፤ መቋሚያውን ፤ እና መሰል መገልገያዎችን ወደ አዳራሾቻቸው ካስኮበለሉ ቆይተዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለአገልጋዮቿ የምትሰጠውን የማዕረግ ስም መጠቀም ከጀመሩም ሰንበትበት ብለዋል፡፡ የቅዱስ ያሬድን ዜማ ቤተ ክርስቲያን ባስተማረቻቸው ሰዎች አማካኝነት አባሎቻቸውን በማስተማር ፍጹም አይን ያወጣ ዝርፊያ በማድረግ እንደ ተሐድሶያውያን መዝሙር መሳይ ዘፈኖቻቸውን መስራት ጀምረዋል ፤ ምንም የግጥምም ሆነ የዜማ ለውጥ ያልተደረገባቸው መዝሙሮቻችን የአዳራሾቻቸው ማሞቂያዎች ከሆኑ ቆይተዋል ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በበገና የታጀበ መዝሙር ለገበያ አቅርበዋል ፤ ስብከቶቻቸው ላይም ስለማያውቁት ቅዱስ ያሬድ በማንሳት ሰማያዊ ጸጋን ከአምላክ መቀበሉን እየሰበኩ ይገኛሉ ፤ .. ታዲያ እኝህ ሰዎች ምን ቀራቸው ? በነገራችን ላይ አሰላ የሚገኙ ፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በ40 እና በ80 ቀን በአዳራሾቻቸው ልጆቻቸውን ክርስትና ማስነሳት መጀመራቸውን ሰምተናል ፡፡ እኔን የገረመ የ40 እና የ80 ቀን በማለት ቤተክርስትያን ልጇቿ የሥላሴ ልጅነትን የምትሰጥበት ትርጉሙን አንብበውም ይሁን ከሰው ጠይቀው ሊያውቁት ይችላል ፡፡ ግን ልጆቹን ሲያጠምቁ ምን አይነት ጸሎት እንደሚያደርጉላቸው ማወቅ ነበር የሚያጓጓው ፤ ማን ያውቃል ያስኮበለሉት አገልጋይ ሊኖርም ይችላል ፡፡ ቄስ በሪሁን የዛሬ ዓመት ከነጋድረስ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ራሱን ሲያስተዋውቅ “ቄስ በሪሁን እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደኩት ወሎ ክፍለ ሀገር ነው፡፡ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርን በአዲስ አበባ እና ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ተከታትያለሁ፡፡ እንደ ማንኛውም ወጣት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነው ያደኩት፡፡ መካነ ኢየሱስ አጠገቤ ስለነበረች የወንጌል ሙቀትን ከሷ ነው ያገኝሁት” በማለት ነበር ራሱን ያስተዋወቀው፡፡ ይህው ሰው ከጌሤም መጽሔት ቅጽ 3 ቁጥር 1 ጥቅምት 2005 ዓ.ም ዕትም ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር፡፡ ቃለ መጠይቁን እንዲህ ነበር ጌሤም፡- የአሁን ወደ አዲስ አበባ አመጣጥ ለእረፍት ነው ወይስ ለተለየ እቅድ አለህ? “እንግዲህ የአሁኑ ጉዞዬ ትንሽ ለየት ያለ ነው ፡፡ በኢቢኤስ ለስምንት ወር ያህል በተከታታይ ስናገርበት የነበረና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአብይ ጾም በአንድነት እንድንጾም በአብይ ጾሙ ዙሪያ ላይ የሚመለከታቸው ሰዎች ለማነጋር 2005ትን አብይ ጾም አብረን በመላው አለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት ስለሀገራችን ፤ ስለህዝባችን ፤ ስለወንዞቻችን ፤ ስለተራሮቻችን ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ ቃለ እግዚአብሔር በሚያዘው መሰረት ወደ እግዚአብሔርፊት በሥላሴ የምናምን በሙሉ እንድንቀርብ ለማስተባበር ነው የመጣሁት፡፡ ይህንን ጉዳይ ብዙ ሕዝብ ሰምቶት አስተያየታቸውንም በስልክ ፤ በኢሜል ለእኔም አሜሪካ ሀገር ባለኝ ኢሜልና አድራሻዬ ስልክ እንዲሁም ደግሞ አዲስ አበባ ባለው ቢሯችን በስልክ ምላሽ ሰጥቷል ፤ ጥያቄዎችንም አብራርቼአለሁ አሁንም ይቀጥላል፡፡ ……….የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ነች ፡፡ ረዥም ዓመት በወንጌል አገልግሎት የቆየች ቤተክርስቲያን ነችና ባህላዊውንም ከወንጌላውያን የተሻለ ዓይነት ሁኔታ ታውቃለች፡፡ ታሪካዊ አመጣጧ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይህን ያህል ዘመን ጸንቶ ፆሙ የመቆየቱ ሁኔታ የጥንካሬው ምክንያት የቤተክርስቲያቱ ሊቃውንቶች ቢያብራሩት ይሻላል፡፡” በማለት መልሷል፡፡ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምን ቀራቸው?
እግዚአብሔር እንዲረዳን ሁሌ ስለቤተክርስቲያን እና ስለ ምዕመናን እንጸልይ:: ይህን የመነቃቃት እና የፍትህ ዘመን ስንናፍቀው ነበር ፤፤ ሁሉም ነገር በጊዜው ነውና እነሆ ዛሬ እውነተኛ አባቶች እንደገና በመፈጠራቸው በጣም ተደስተናል ፡፡ ቤተክርስቲያን የተዋረደችበትና በአደባባይ ስማ እየተነሳ መሳለቂያ የሆነችበት እንደዚህ ያለ ዘመን ከቶ የለም ፤ አላታየም ፡፡ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ ፤ የመሬት መነጠቅ፤ የካህናት መገደል(መታረድ) ፡ የምዕመናንን መገደል (መታረድ) ፤ የአምልኮ ቦታ መከልከል…………. ፤፤ ይሄ ሁሉ በደል እንዴት አንድ ህግ ባላት ሀገር ውስጥ ይፈጸማል // ይህም የሆነው ለቤተክርስቲያን እና ለምዕመናን የቆመ እና ሰማያው የሆነውን አባታዊ አደራውን የረሱ አባቶቸ ስለተበራከቱ ነው ፡፡ እናንተን እውነተኛ አባቶቸን ግን እግዚአብሄር ስለሰጠን ኮርተንባችሀል ፡፡በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን ህልውናዋ እና መብታ እንዲረጋገጥ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያለ ቆራጥ መሪ እና ለእውነት የቆመ አባት ያስፈልገናል ፡፡አቡነ ጴጥሮስን ታሪክ የሚዘክራቸው አባት ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸውን ስለእውነት አሳልፈው ስለሰጡ ጭምር ነው ፡፡... እባካችሁ አባቶች ይህ በደል እና ግፍ ታስቦ እና ተቀነባብሮ ቤተክርስቲያን ለማዳከምና ህልውናዋን አደጋ ላይ ለመጣል ሆን ተብሎ በሁሉም ቦታ እየተሰራ ያለ ሴራ ስለሆነ እውነተኛ ፍትህ እስክታገኙ ድረስ ወደ ኀላ እንዳትመለሱ ፡፡ በመድረኩ ላይ ያልተነሱ ብዙ ከባድ እና አስከፊ በደሎችም ስላሉ ወደ ታች ወርዳችሁ ምዕመናንን ማማከር እንዳትዘነጉ ፡፡ ይህ ነገር የአንድ ሰሞን ግርግር ብቻ ሆኖ እንዳይቀር አደራ እላለው ፡፡ ምእመናንም ይህንን ግፍ በዝምታ እና በትዕግስት ማለፍ ይብቃን እላለው ፡፡ ህግ ባላት ታላቅ ሀገር ስላላን የህግ ያለህ እንበል /// ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡ በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም›) እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው››) አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡››)አለቻት አሉ፡፡

No comments:

Post a Comment